በአብራሀሚክ ጋረድን ልማትና የባለድርሻ አካላት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

በአብራሀሚክ ጋረድን ልማትና የባለድርሻ አካላት ሚና ላይ አውደ ጥናት ተካሄደ

በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል እየለማ በሚገኘው የአብራሀሚክ ጋርደን የዕድገት ሁኔታ እና  የባለድርሻ አካላት ሚና ላይ አውደ ጥናት ተካሄደ፡፡በአውደጥናቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከሉ የምርምር ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ የአበረሀም ልጆች ሀየማኖቶች የሆኑት የክርስትና ፣ የእስልምናና የጁዲዝም ዕምነቶች ሰላምን እንደሚያስቀድሙ ጠቅሰው ለዕፅዋት እንክብካቤና ጥበቃ የበኩላችውን ሚና ከጥንት ጀምሮ እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡በመሆኑም የአብረሀሚክ ጋርደን በማዕከሉ ሲቋቋም ሶስቱም ዕምነቶች የሚንከባከቧቸውን ዕፅዋት ወደ ማዕከሉ በማምጣት የመጠበቅና የመንከባከብ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን ከመሰረቱት ምሁራን መካከል ግንባር ቀደም የሆኑት ታዋቂው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው በበኩላቸው ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ እና የጥንት ቀደመስልጣኔ ባለቤትም መሆኗን ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ገልፀው እነዚህን ሀይማኖቶችንም  ቀድማ የተቀበለች ሲሆን ቤተእምነቶቹ ዕፅዋትን በአፀዳቸው የመንከባከብ ልማድ እንዳለቸው ዓብነቶችን እያጣቀሱ አቅርበዋል፡፡ በሌሎች ሁለት ተመራማሪዎች በዘርፉ ላይ ጥናታዊ ፁሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡በመጨረሻም የአውደጥናቱ ተሳታፊዎች እየለማ የሚገኘውን የአብራሀሚክ ጋርደንን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡