በብዝሀ-ህይወት ትምህርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

በብዝሀ-ህይወት ትምህርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በብዝሀ-ህይወት ትምህርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ  ከባለለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡በማዕከሉ የብዝሀ-ህይወት ትምህርት ዳየሬክቶሬት በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ ቁጥራው  ከአርባ በላይ የሆኑ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ከሌሎች የተምህርቱ ማህበረሰቡ የተወከሉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡አውደጥናቱን በንግግር የከፈቱት የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዳይሬከተር አቶ ሞገስ አባተ ተሳታፊዎቹን ወደ ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል እንኳን በደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ የዕፅዋት ማዕከሉ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በዝርዝር አሰረድተዋል፡፡ማዕከሉ ከትምህርቱ ማህበረስብና ከትምህርት ቤቶች ጋር በቅርበት ለመስራትና ተማሪዎች ወደ ማዕከሉ በብዛት እንዲመጡና ተግባር ተኮር የብዝሀ-ህይወት ትምህርት እንዲያገኙ  እየሰራ መሆኑን ገልፀው ለተግባራዊነቱ ሁሉም በእኔነት መንፈስ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡በብዝሀ-ህይወት ዳይሬክቶሬት ዳዳይሬክተር በአቶ ዮሀንስ መላኩ እና በባለሙያው በአቶ እሸቱ ወርቁ ሁለት ጥናታዊ ፁህፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ውይይቱን የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ እና የምርምር ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ መርተውታል፡፡