የዕፅዋት ማዕከላት ለተፈጥሮ ጥበቃና ለቱሪዝም ዕ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

የዕፅዋት ማዕከላት ለተፈጥሮ ጥበቃና ለቱሪዝም ዕድገት ባላቸው ሚና ላይ የፓናል ውይይት ተካሄደ

በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የዕፅዋት ማዕከላት ለተፈጥሮ ጥበቃና ለቱሪዝም ዕድገት ባላቸው ሚና ላይ የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡የፓናል ውይይቱ በማዕከሉ ከህዳር 27- 29 /2018 ዓም በልዩልዩ ዝግጅቶች የተካሄደው የታላቁ ሁነት አካል ነው፡፡በፓናሉ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ጉተማ ሞሮዳ ተሳታፊ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣቹ ካሉ በኃላ የፓናል ውይይቱ ለዕፅዋት ማዕከሉ  ቀጣይ ልማት ፋይዳ ይኖረዋል በማለት ፓናሉን በይፋ አስጀምረዋል፡፡ታዋቂው የዘርፉ ተመራማሪና የአዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ፕሮፌሰር ዘሪሁን ወልዱ እና የቱሪዝም ተመራማሪው ዶክተር ኤፍሬም አሰፋ የዕፅዋት ማዕከላት ለተፈጥሮ ጥበቃና ለቱሪዝም ዕድገት ባላቸው ሚና ላይ የውይይት መነሻ ፁህፎችን አቅርበዋል፡፡የማዕከሉ ዋና ዳይረክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ ከየፁሁፍ አቅራቢዎቹ ጋር በመሆን ውይቱን መርተውታል ፡፡ በውይይቱ ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች  የተሰጡ  ሲሆን ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵ በተ-መፃፍትና ቤተ-መዘክር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰርፀ ፍሬሰንበት ባስተላለፉት መልዕክት ኤጀነሲው ዕፅዋትና ከዕፅዋት ጋር ተያያዥነት ያለቸውን መፅሀፍት በማሰባሰብ ላይ ሞኑን ገልፅው በቀጣ በምከሉ ቤተ መፅሀፍት በመክፈት ለንባብ እንደሚያበቃ ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም የሶስት ቀኑ ሁነት እንዲሳካ ላደረጉ ተቋማትና ለተቋሙ  ብራንድ አምባሳደር ተጓዥ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የዕውቅናና የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቷል፡፡