የማዕከሉ አራቱ ዓላማ ፈጻሚዎች የህዳር ወር የስራ አፈጻጸም እና በማዕከሉ ስለተካሄደውን ሁነት ሪፖርት ቀረበ
የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ዓላማ ፈጻሚዎች በህዳር ወር ያከናወኑትን ተግባራት እና በማዕከሉ ለሶስት ቀናት የቆየውን ሁነት በተመለከተ የማዕከሉ ጠቅላላ ካውንስል አባላት በተገኙበት ሪፖርት ቀረበ፡፡
የዓላማ ፈጻሚዎቹን የህዳር ወር ሪፖርት የማዕከሉ ዕቅድና በጀት ክትትል ግምገማ ዝግጅት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ምስክር ታዬ አቅርበዋል፡፡
በመቀጠል ከህዳር 27 - 29 2018 ዓ.ም የተዘጋጀውን ሁነት የኢኮቱሪዝም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳንኤል አማረ ያቀረቡ ሲሆን በሁነቱም ላይ የተራራ መውጣት፤ የዱር አዳር ፕሮግራም፤ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ፤ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የፓናል ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞረዳ ባደረጉት የማጠቃለያ ሃሳብ በቀረበው የህዳር ወር ሪፖርት ላይ በሰጡት ሃሳብና አቅጣጫ መሰረት ለቀጣይ መስተካከል ያለባቸውን ነጥቦች በማንሳት ከክፍሎቹ ኃላፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ሁነቱን በተመለከተ ማዕከሉን ለማህበረሰቡ ከማስተዋወቅ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳደረገ በመግለጽ ይህንን ሁነት እንዲሳካ ላደረጉ ለኢኮቱሪዝም ክፍል ባለሙያዎች በሙሉ ከፍተኛ ምስጋናቸውን በማቅረብ የዕለቱን አጀንዳ ተጠናቋል፡፡