ለማዕከሉ ከፍተኛና መካከለኛ ባለሙያዎች ሲሰጥ የ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

ለማዕከሉ ከፍተኛና መካከለኛ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለተከታታይ 10 ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኮቱሪዝም ልማት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሞገስ አባተ በዚህ ስልጠና ላይ ሰራተኛው ያስፈልጋሉ ተብለው በተመረጡ ርዕሶች ላይ የተዘጋጀ በመሆኑ በንቃት መከታተል እና ወደ ስራ ቦታችን እና ወደ ህይወታችን አምጥተን ልንተገብረው እንደሚገባ በመግለጽ ስልጠናውን አስጀምረዋል፡፡ 
ስልጠናውን ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በተጋበዙ በዶ/ር ምህረት  ገ/መስቀል እና በዶ/ር ተስፋዬ ኢባ ከሰፊ ሙያዊና አሳታፊ ከሆኑ የህይወት ተሞክሮዎች ጋር ስለ አገልግሎት አሰጣጥ፤ አፈጻጸም አመራር፤ የተግባቦት ክህሎት እና የባህሪ ግንባታ ላይ ትኩረቱን በማድረግና ከሰራተኛው የግንዛቤና የስራ ድርሻ ጋር በማጣጣም ለሰራተኛው ተሰጥቷል፡፡
ይህን ስልጠና ሰራተኛው ከመውሰዱ በፊት እና በኋላ ያገኘውን እውቀት ለመለካት የሚያስችል የመግቢያና የመውጫ ፈተና በስራ ክፍሉ በማዘጋጀት የሰራተኛውን የግንዛቤ መጠን ለመለካት ተችሏል፡፡
በመጨረሻም የማዕከሉ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ አበበ ባደረጉት ንግግር ይህን ስልጠና እንዲዘጋጅና በተሳካ መልኩ እንዲሰጥ ላደረጉት የማዕከሉ አመራሮች ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ የዕለቱን የመዝጊያ ንግግር የማዕከሉ የዕፅዋት ምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደበላ ብሩ ከዚህ ስልጠና የተገኘውን ዕውቀት ማዕከሉ ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ በቁርጠኝነት መጠቀም እንደሚገባ በመግለጽ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡