ቋሚ ኮሚቴው የማዕከሉን የግማሽ አመት አፈፃፀም...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- Recent News   

ቋሚ ኮሚቴው የማዕከሉን የግማሽ አመት አፈፃፀም የሚያበረታታ ነው አለ

የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የ2018 ዓ.ም በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም የሚያበረታታ ነው ተባለ፡፡የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሬትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መስክ ላይ በመገኘት የማዕከሉን ሥራዎች ተዘዋውሮ ከተመለከተ በኃላ ከማዕከሉ የማኔጅመንት አባላት ጋር ባደረገው ውይይትና በሰጠው ግብረመልስ አፈፃፀሙ የሚያበረታታ መሆኑን ገልፃል፡፡የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር አቶሜ አበበ እንዳመለከቱት ኮሚቴው ትኩረት አድርጎ የተመለከታቸው የችግኝ ማባዛት፣የዕፅዋት እንክብካቤ፣የሌብሊንግ፣ የማስታወቂያ ሥራዎች ዕምርታ ማሳየቱን ፣የሥራዕድል ፈጠራ ማደጉን፣የጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር የተሰሩ በርካታ ሥራዎች መኖራቸውን እና የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችም በተወሰነ መልኩ መሻሻል ማሳየታቸው አፈፃፀሙን የሚያበረታታ አድርገውታል ብለዋል፡፡የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ትኩረት የሚሹ ስራችዎን ለይቶ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ፣ የኢኮቱሪዝም ሥራዎችን የበለጠ ማስተዋወቅ፣ሁነት ሲዘጋጅ ከወቅቱ ጋር የተናበበ እንዲሆን ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡ የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ጉተማ ሞሮዳ ቋሚ ኮሚቴው የሰጣቸውን አስተየየትና ምክር ማዕከሉ በቀጣይ ለሚሰራቸው ስራዎች ግብዓት እንደሚሆኑት አመልክተው የማዕከሉን ሥራዎች እና እያጋጠሙት ያሉትን ተግዳሮቶች ለቋሚ ኮሚቴው በሰፊው አስረድተዋል፡