በወርቃማ ሰኞ ምርጥ የህይወት ተሞክሮ በማዕከሉን የዕፅዋት ምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ቀረበ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የዕፅዋት ምርምር ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደበላ ብሩ የዛሬውን ወርቃማ ሰኞ እጅግ በጣም አስተማሪና ሌላው ሰራተኛ ቢጠቀምበት ግብዓት ሊሆኑ በሚችሉት ላይ የህይወት ተሞክሯቸውን አቀረቡ፡፡
አቶ ደበላ ብሩ ራሳቸውን ከማስተዋወቅ ጀምረው በትምህርት እና በስራ ዘመናቸው ያሳለፉትን ውጣ ውረድ እና የደረሱበትን ስኬት ለሰራተኛው አካፍለዋል፡፡ በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርታቸውን በመጀመሪያ ዲግሪ በፊዚክስ እና ሁለተኛ ዲግሪ በአካባቢ ሳይንስ መመረቃቸውን ገልጸዋል፡፡
በመቀጠል ለአብዛኛው የማዕከሉ ሰራተኞች ከዚህ በፊት የማያውቁትን እና የተደነቁበትን አስገራሚ የሆነውን
- Fundamental concepts of secondary school physics grade 9 and10 (1999 E.C)፣
- ALPHA quick reference for preparatory programme (1999 E.c)፣
- Omega joint Revision work (grade 7 and 8 ) (1999)
- Comet supplementary Series: Physics grade 9 and 10 (2007-2014 E.C)
- Physics grade 9and10 (2016 E.C)
የተባሉ መጻህፎችን አሳተመው ለአገልግሎት ማብቃታቸውን ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ ተግባር ተኮር ቡክሌቶችን በማዘጋጀት ለሀገር እንዲሁም ለነገ ሀገር ተረካቢዎች ግንባታ የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል፡፡ አቶ ደበላ ብሩ በስራ ዘመናቸው በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ላይ የሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ከሰራተኛው እጅግ ከፍተኛ አድናቆትና እንደ ዜጋ ለሀገራቸው ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ሰራተኛው ምስጋናውን አቅርቧል፡፡