በጥብቅ ሥፍራ ደህንንነት አጠባበቅ ላይ ለሬንጀርስ ስልጠና ተሰጠ
የኢትዮጵያ ዱር እንሰሳ ጥበቃ ባለስልጣን ከኦሮሚያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ጋር በመተባበር ከሀገሪቱ ብሄራዊ ፓረኮች ለተውጣጡና ከጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ለሄዱ ሰልጣኞች(RANGERS) በጥብቅ ሥፍራ አጠባበቅ ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡በስልጠናው ላይ የማዕከሉ የጥበቃ አስተባባሪዎች የሆኑት አቶ ክንፈ ገብረማሪያምና አቶ ተስፋዬ ደገፋ ተሳተፈው በሰርተፊኬት ተመርቀዋል ፡፡ ስልጠናው ለአንድ ወር ወይም ለ198 ሰዓት የተሰጠ ሲሆን ከ22 ፓርኮች ለመጡ 105 ሬንጀርስ ተሰጥቷል፡፡በክፍል ውስጥ ስልጠናው ካተታቸው ርዕሰጉዳዮች ስነምግባር፣ሰባዊመብት፣ህገ-መንግስት፣የተቋም ጥበቃ፣ኮሚኒቲ ፖሊሲንግ፣መረጃ አያያዝና ሚስጥር አጠባበቅ እና መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ሲሆኑ በመስክ ደግሞ ወታደራዊ እንቅስቃሴ፣ የአካል ብቃት፣እንግዳ አቀባበል፣የቪ.አይ.ፒ እጀባ እና ኢላማ ተኩስ ናቸው፡፡