ጠቅላላ ካውንስሉ የማዕከሉን የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገም
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ጠቅላላ ካውንስል የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ገመገመ፡፡የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ በተገኙበት የአራቱ አላማ ፈፃሚ ዳይሬክቶሬቶች እና የስታዳርዳይዜሽን ዝግጅትና አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ ቡድን ሪፖርቱን አቅርበዋል፡፡በዚህም የዕፅዋት ምርምር ልማት ፣ የሆርቲካልቸር ልማት፣የብዝሀ ህይወት ትምህርት እና የቱሪዝም ልማትና ፕሮሞሽን ልማት ዳይሬክቶሬቶች አፈፃፀሙን በዝርዝር አቅርበው የጠቅላላ ካውንስሉ አባለት ሰፊ አስተያየትና ጥያቄዎች አንስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ሪፖርቱ በቅርቡ ለጠቅላላ ሰራተኛው ቀርቦ የጋራ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡