ሠራተኛው መብትና ግዴታውን ማወቁ ለስራው ውጤታማነት ይጠቅመዋል ተባለ
ሠራተኛው መብትና ግዴታውን ማወቁ ለስራው ውጤታማነት ይጠቅመዋል ተባለ፡፡የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ሠራተኞች ዛሬ ወርቃማ ሰኞን አስመልክተው ባደረጉት ስብሰባ ላይ የማዕከሉ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ አበበ ባቀረቡት ሰነድ ላይ የሠራተኛውን መብትና ግዴታ በሰፊው አብራራተዋል፡፡በመሆኑም በሥራ የበለጠ ውጤታማ ለመሆንና ተቋሙንም ለማሳደግ የሚቻለው መብትና ግዴታን በእኩል ማየትና መተግበር ሲቻል ነው ብለዋል፡፡