የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ አጋራ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ አጋራ።በማዕከሉ የሚረዱ አቅመ ደካማ ወገኖች ለገና በዓል የተዘጋጀላቸውን የማዕድ ማጋራት ስጦታ ከማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ከአቶ ሞገስ አባተ እጅ ተቀብለዋል፡፡በዚህም ቁጥራቸው አስራሶስት ለሚሆኑ በማዕከሉ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ወገኖች ለእያንዳንዳቸው 15 ኪሎ ጤፍ ፣ 3ሊትር ዘይትና 14 ዕንቁላል ማዕድ ተጋርቷል ።በተጨማሪም አካል ጉዳተኛና የአእምሮ ውስንነት ላለበት ልጅ እናት ከሠራተኛው የተዋጣ የ20,500 ብር ድጋፍ ተደርጓል ።