የማዕከሉ የግማሽ በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም አበረታች ነው ተባለ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በእጅጉ የሚያበረታታ ነው ተባለ፡፡ የአፈፃፀም ሪፖርቱ የማዕከሉ ከፍተኛ አመራሮችና ጠቅላላ ሰራተኞች በተገኙበት ከቀረበ በኃላ በርካታ አሰተያቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ ውይይቱን ሲያጠቃልሉ የግምሽ አመቱ የማዕከሉ ዕቅድ አፈፃፀም በእጅጉ የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡ዋና ዳይሬክተሩ በምርምር ልማት፣በሆርቲካልቸር፣ በብዝሀ ህይወት ትምህርት እና በኢኮቱሪዝም ዘርፎች ታቅደው የተከናወኑት ሥራዎች በቀጣይ ለሚሰሩት መሰረት የጣሉ በመሆናቸው በሁለተኛው ግማሽ ዓመት ከዚህ የበለጠ ስኬት ለማሰመዝገብ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡በግማሽ በጀት ዓመቱ ለተመዘገበው ስኬት የሥራ ክፍሎች ተመጋግበውና ተናበው መስራታቸው ትልቅ ሚና ሰለነበረው ይሄንን ባህል አድርገን መቀጠል አለብን ብለዋል፡፡ ሪፖርቱን የማዕከሉ የዕቅድ፣በጀት፣ድጋፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ምስክር ታዬ ያቀረቡ ሲሆን የማዕከሉ የምርምር ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ እና የኢኮቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር በመሆን ውይይቱን መርተውታል፡፡