ማዕከሉ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ሠራተኞቹን በከተማ ግብርና ቱርፋት ተጠቃሚ እንዳደረገ ገለፀ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በ2018 ዓም በጀት ዓመት በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ሠራተኞቹን በከተማ ግብርና ቱርፋት ተጠቃሚ እንዳደረገ ተገለፀ፡፡የማዕከሉ የሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መክብብ ማሞ እየለማ ካለው የከተማ ግብርና ቱርፋት ሠራተኛው ባለፉት ስድስት ወራት በአምስት ዙር የተመረቱ በርካት የአትክልት ዓይነቶች ተጠቃሚ ሆኗል ብለዋል፡፡
በዚህም በገበያ ዋጋቸው ሲሰላ ከስድት መቶ ሰላሳ ሺ ብር በላይ የሚሆኑ የአትክልት ዓይነቶች ለቋሚ ፣ለኮንትራትና ለጊዜያዊ ሠራተኞች አምስት ጊዜ ማከፋፈል መቻሉን ገልፀዋል፡፡የከተማ ግብርናው ቀደም ብሎ በ0.84 ሄክታር ላይ የተጀመረ ቢሆንም በቅርቡ በተሠራው የማስፋፊያ ሥራ ወደ 1.35 ማሳደግ መቻሉን ኃላፊው ቸምረው ገልፀዋል፡፡