ለማዕከሉ ሰራተኞች በስነምግባርና ፀረሙስና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
ለጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች በጥቅም ግጭት ላይ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የማዕከሉ የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኤሊያስ ከበደ ለአጠቃላይ የማዕከሉ ሰራተኛ ግንዛቤ እንዲያገኝ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን በመግለፅ ስልጠናውን ከፍተዋል፡፡
ስልጠናውን ከአዲስ አበባ ስነምግባርና ፀረሙና ኮሚሽን የስልጠና ዳይሬክቶሬት የመጡት አቶ ተሾመ ጌዴቦ ስለጥቅም ግጭት ምንነት፤ የጥቅም ግጭቶች ስለሚከሰቱባቸው መንገዶች፤ የጥቅም ግጭት አይነቶች፤ የጥቅም ግጭት ገጽታዎች እና በሙስና እና በጥቅም ግጭት መካከል ያለውን አንድነት እና ልዩነት በተመለከተ ስልጠናውን ለሰራተኛው ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም በዕለቱ በቀረበው ርዕስ ከሰራተኛው የተነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠትና እንዲወያዩ በማደረግ የዕለቱን መድረክ ተጠናቋል፡፡