በብዝሀ-ህይወት ትምህርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ
በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በብዝሀ-ህይወት ትምህርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከባለለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡በማዕከሉ የብዝሀ-ህይወት ትምህርት ዳየሬክቶሬት በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አነጂነር ጉተማ ሞሮዳ ተሳጣፊዎቹን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ ማዕከሉ በዘርፉ እያከናወናቸው ያሉትን የዕፅዋት ልማት ሥራዎች በዝርዝር አብራራተዋል፡፡ የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጥሪ የተደረገላቸው ረዕሰ መምህራን ሲሆኑ በአውደ ጥናቱ ላይ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሳምሶን ተገኝተዋል በብዝሀ-ህይወት ዳይሬክቶሬት ዳዳይሬክተር በአቶ ዮሀንስ መላኩ እና በባለሙያው በአቶ እሸቱ ወርቁ ሁለት ጥናታዊ ፁህፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ውይይቱን የማዕከሉ የኢኮቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አባተ እና የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሳሚሶን መለሰ መርተውታል፡፡