የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት ሠራተኞች የአብሮነት ቀንን በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አከበሩ
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት ሠራተኞች የአብሮነት ቀንን በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አከበሩ፡፡ የተቋሙ ሠራተኞች የማዕከሉ ችግኝ ጣቢያ ሲደርሱ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ተቀብለው እንኳ የአዲስ አበባ አረንጓዴ ሳንባ ወደ ሆነው ወደ ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በደህና መፃችሁ ካሉ በኃላ ማዕከሉ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ገልፀዋል፡፡የኢኒስቲትዩቱ አመራሮችና ጠቅላላ ሠራተኞች በማዕከሉ የደርሶ መልስ የ10 ኪሎሜትር የጫካ ውስጥና የተራራ ላይ የእግር ጉዞ በማድረግ የአብሮነት ቀንን በጋራ አክብረዋል፡፡ከእግር ጉዞው በኃላ በተደረገ የውይይት መድረክ የኢኒስቲትዩቱ ዋና ደይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ አብሮነት የሥራ መንፈስን ለማጠንከር የሚረዳ ኃይል ነውና እንዲህ በጋራ ሰናስበው ለቀጣይ ሥራዎቻችን ጉልበት ይሆነናል ብለዋል፡፡