የመንግስትን ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ተገለፀ
የመንግስት ሀብትና ንብረት በአግባቡ ጥቅም ላይመዋል እንዳለበት ተገለፀ፡፡መልዕክቱ የተላለፈው ዛሬ ወርቃማው ሰኞ ላይ በተካሔደ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡የማዕከሉ የውጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አየለች ባየልኝ ባቀረቡት ሰነድ የመንግስትን ሀብትና ንብረት እንዴት በተቀመጠው መመሪያ መሰረት በአግባቡ ጥቅም ላይ ይውላሉ? ለብልሹ አሰራር እንዳይገለጡ እንዴት መከላከል ይገባል ? ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ አሰራሮች ሲከሰቱ ምን መደረግ አለባቸው በሚሉትና እና በተያያዝ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡