በዛሬው ወርቃማ ሰኞ ላይ በህንጻ አስተዳደርና አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀረበ፡፡
የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የህንጻ አስተዳደርና ጥገና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሚኪያስ ሀብቱ በዛሬው የወርቃማ ሰኞ ላይ በህንጻ አስተዳደርና አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ሰነድ አቀረቡ፡፡
ካቀረቡት ሰነድ ውስጥ የመንግስት እና የህዝብን ንብረት እንዴት መጠበቅ እንደምንችል፣ ንብረቶችን ትክክለኛ አስተዳደር፣ ዘመናዊ የአጠባበቅ ዘዴዎች ላይ በመመርኮዝ በቪዲዬ በታገዘ ገላጭ እና አስተማሪ የሆነ ግንዛቤ ማስጨበጫ አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም አቶ ሚኪያስ የራሳቸውን የትምህርት እና የህይወት ተሞክሮ ለሰራተኛው ያካፈሉ ሲሆን በዋናነት በማዕከሉ ውስጥ ያሳረፉትን አሻራ የቀድሞውን እና የአሁኑን የማዕከሉ ገጽታ በምስል በማነጻጸር ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም ሁሉም በተሰማራበት የስራ ድርሻ የበኩሉን እንዲወጣ ሀሳባቸውን በመስጠት የዕለቱን አጀንዳ አጠናቀዋል፡፡