ከሶሻል ሚዲያ በተገኘ ርዕስ ላይ ያተኮረ የወርቃ...

image description
- Recent News   

ከሶሻል ሚዲያ በተገኘ ርዕስ ላይ ያተኮረ የወርቃማው ሰኞ መድረክ በደማቅ ድባብ ተካሄደ

ከሶሻል ሚዲያ በተገኘ ርዕስ ላይ ያተኮረ የወርቃማው ሰኞ መድረክ በደማቅ ድባብ ተካሄደ፡፡ የዕለቱን የወርቃማ ሰኞ የማነቃቂያ ፕሮግራም የማዕከሉ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያሬድ ጌታሁን ለውሳኔ አለመቸኮል፤ በማንኛውም ጉዳዩ በማይመለከተን ቦታ ጣልቃ አለመግባት እና በተረጋጋ መንፈስ ስራችንን ማከናወን እንዳለብን አሁን ሰራተኛው ካለበት ከነባራዊ የስራ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ከሶሻል ሚዲያ ያገኙትን ርዕስ ለሰራተኛው አቅርበዋል፡፡
በመቀጠል የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ  በስራ ቦታችን ላይ ስራዎችን በቀጥተኛ መንገድ መስራት ፣ ውሳኔ ለመስጠት መረጃና ማስረጃ ማሰባሰብ እንደሚስፈልግ እና የቀረበውን ሃሳብ የሚያጠናክሩ መልዕክቶችን በመጨመር ሶሻል ሚዲያ በአዎንታዊ መንገድ መጠቀም  እንደሚያስፈልግ በመግለጽ የዕለቱን መድረክ ተጠቃለዋል፡፡