የዓድዋ አደራ አንድነት ሉዓላዊነት እና ማንሰራራት በሚል ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ኮሙኒኬሽን
ቀን 9/6/2018 ዓ.ም
አድዋ ድል 130ኛ ዓመትን አስመልክቶ የአድዋ አደራ አንድነት እና ማንሰራራት በሚል ሰነድ ላይ ውይይት ተደረገ
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት የአድዋ ድል 130ኛ ዓመት አከባበርን የተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ፡፡ የዕለቱን የመክፈቻ ንግግር የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ ያደረጉ ሲሆን በመክፈቻው ላይም ዓድዋ የመላው የጥቁሮች ህዝብ ኩራት እንደሆነ እና በዋናነት የዚህ ድል ባለቤት ሀገራችን ኢትዮጲያ በመሆኗን ታላቅ ኩራት ይሰማናል በማለት መድረኩን አስጀምረዋል፡፡
በመቀጠልም ሰነዱ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ ውስጥ ዛሬ የምናከብረው ዓድዋ ድል በዓል ድሉ ከትላንቱ የዓድዋ ጦርነት ባሻገር ለዛሬው ሀገራዊ ግንባታና ለነገው የብሔራዊ ከፍታ እንደ መነሻ ሊያገለግልና ልንጠቀምበት ይገባል በሚል ሃሳብ ላይ ሰፊ ትንታኔ ተካቷል፡፡
የበለጸገች ኢትዮጲያን እውን ለማድረግ ከአሁኑ ትውልድ ምን ይጠበቃል በሚል በሰነዱ ውስጥ ለተካተተው ሃሳብ የኢትዮጲያን የብልጽግና ጉዞ ዕረፍት የነሳቸው እና እንደ ስጋት የሚቆጥሩን ሃይሎችን የኢትዮጲያን ሕዝብ በተለያየ የሀሰት ትርክት በመከፋፈል እርስ በእርሳችን እንዳንተማመን እና በአንድነት እንዳንቆም ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ በሚገኙ ላይ እንደ ሃገር የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ጠንካራ ሕዝባዊ አንድነት እና ሀገራዊ ስሜት መፍጠር አማራጭ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ወቅት ላይ በመሆናችን የዓድዋ ጀግኖች በአንድነትና በሀገር ፍቅር ስሜት ጠላትን ድል እንዳደረጉት ሁሉ እኛም ከባዳ እና ከባንዳዎች የሚሰነዘርብንን የጥፋት ጦር በአንድነት እና በተባበረ ክንድ መቀልበስና የኢትዮጲያን ከፍታ እውን ማድረግ እንደሚገባን ተብራርቷል፡፡
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ ከሰራተኛው የተለያዩ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ማጠቃለያውን የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር የሥራ ባህላችንን በመቀየር ፤ብሄራዊ ጥቅማችንን በማወቅና በማስከበር ፣የኢኮኖሚ ሉአሏዊነታችንን በማረጋገጥ ፣ እና ተባብረን በመስራት ሀገራችንን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ እንዳለብን በመግለጽ የዕለቱን መድረክ ተጠናቋል፡፡