የብዝሀ-ህይወት ትምህርት ለተማሪዎች ተሰጠ
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ከጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመጡ ተማሪዎች በተግባር የተደገፍ የብዝሀ-ሕይወት ትምህርት ሰጠ፡፡የማዕከሉ የብዝሀ-ህይወት ትምህርት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ቁጥራቸው መቶ ለሚሆኑ ከዘጠነኛ እስከ አስራሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርቱን በተግባር ሰጥተዋል፡፡በዚህም አበባ ያላቸው ከሌላቸው እንዴት ይለያሉ፣የመከለያ ቤት ጠቀሜታው፣ ስለበረሀማ ዕፅዋት ምንነት፣ ስለችግኝ ጣቢያ አገልግሎት ፣ የዕፅዋት ብዜትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ባለሙያዎቹ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተማሪዎቹ በኩል ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡