ከእንሰሳት የቡድንና የህብረት አኗኗር ምን እንማ...

image description
image description
image description
- Recent News   

ከእንሰሳት የቡድንና የህብረት አኗኗር ምን እንማራለን ? በሚል ውይይት ተካሄደ

የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች በታደሙበት የወርቃማ ሰኞ የውይይት መድረክ ላይ ከእንሰሳት የቡድንና የህብረት አኗኗር ምን እንማራለን የሚል ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሄደበት፡፡በቱሪዝም ልማትና ፕሮሞሽን ዳይሬክቶሬት የቱሪዝም ልማትና ጥናት ቤድን መሪ አቶ መንግስቱ አበራ በእንሰሳት ፣አዕዋፋት እና ነብስቶች አኗኗር ላይ የተደረጉ ጥናቶችን መሰረት አድርገው በቡድንና ብህብረት ያላቸው የአኗኗር ዜዬን በሰፊው አብራርተዋል፡፡የቡድን መሪው ባቀረቡት የመነሻ ኃሳብ ላይ ከእንሰሳቱ የጋራ አኗኗር ላይ እኛ ምን እንማራል? በሚል ከቤቱ በርካታ ጥያቄና አሰተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጉተማ ሞሮዳ ከእንሰሳቱ የጋራ አኗኗር የቡድን ሥራ ለተሻለ ውጤት እና ስኬት እንደሚያበቃ ያስተምረናልና ልንወስደው የሚገባ ተሞክሮ ነው ብለዋል፡፡